ቀጥታ፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ለተሾሙት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 9/2017(ኢዜአ)፦ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ለተሾሙት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ላቭሮቭ ከአዲሱ የውጭ ጉዳይ ተሿሚ ጋር የኢትዮጵያ እና የሩሲያን ለረጅም ጊዜ የቆየ ትብብር በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በሰብዓዊ ጉዳዮች እና በሌሎች መስኮች ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ትብብሩ የሁለቱን ሀገራት ሕዝቦች ተጠቃሚነት እንዲሁም በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ያላቸውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) በስራ ቆይታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ላቭሮቭ መልካም ምኞታቸውን መግለጻቸውን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም