አራተኛው የብሪክስ ዋና አስተባባሪዎች እና ምክትል አስተባባሪዎች ስብሰባ በሩሲያ ካዛን መካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
አራተኛው የብሪክስ ዋና አስተባባሪዎች እና ምክትል አስተባባሪዎች ስብሰባ በሩሲያ ካዛን መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 9/2017(ኢዜአ)፦ አራተኛው የብሪክስ ዋና እና ምክትል አስተባባሪዎች ስብሰባ በሩሲያ ካዛን እየተካሄደ ነው።
በወቅቱ ሊቀመንበር ሩሲያ እየተመራ ባለው ስብሰባ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ እና የኢትዮጵያ የብሪክስ ጉዳይ ምክትል አስተባባሪ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በመሳተፍ ላይ ይገኛል።
በዚህ ስብሰባ ዋና አስተባባሪዎች እና ምክትል አስተባባሪዎች የካዛን ረቂቅ ስምምነት ማዘጋጀት እና የብሪክስ አጋር አገራት አሠራር ማዘጋጀት ላይ አተኩረው እንደሚሰሩ ተገልጿል።
16ኛው የብሪክስ አባል አገራት የመሪዎች ጉባዔ ከጥቅምት 12 እስከ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. በሩሲያ ካዛን ከተማ እንደሚካሄድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።