ቀጥታ፡

በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የምግብ ሉአላዊነትን ለመጎናጸፍ የሚያስችሉ ናቸው

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 8/2017(ኢዜአ)፦በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የምግብ ሉአላዊነትን ለመጎናጸፍ የሚያስችሉ መሆናቸውን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ።

"ሉዓላዊነት በምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣የግብርና ሚኒስቴር፣ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት በመተባበር ያዘጋጁት የፓናል ውይይት በአዳማ እየተካሄደ ነው።


 

በመድረኩ ላይ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር)፤ የምግብ ሉአላዊነት ማእቀፍ በኢትዮጵያ በሚል የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል።

በማብራሪያቸውም የምግብ ሉአላዊነት ከነጻነት ጋር የሚቆራኝ በራስ የመወሰን አቅምን የማረጋገጥ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል።

በምግብ እራሱን ያልቻለና በተረጅነት ላይ ጥገኛ የሆነ አገር የተሟላ ነጻነት አይኖረውም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፥ በኢትዮጵያ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት ውጤት እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል።

በግብርናው ዘርፍ ከፖሊሲ ማሻሻል ጀምሮ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የምግብ ሉአላዊነትን ለመጎናጸፍ የሚያስችሉ መሆናቸውን አንስተዋል።

የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ በግብርናው ዘርፍ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥረው ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውንም ተናግረዋል።

የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ ምርታማነትን በዘላቂነት እየጨመሩ መቀጠል እንደሚገባም አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም