ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሹመቶችን ሰጡ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዛሬው እለት ሹመቶችን ሰጥተዋል።

በዚሁ መሠረት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሰላማዊት ካሳ የቱሪዝም ሚኒስትር እንዲሁም ሃና አርዓያሥላሴ የፍትሕ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) የፍትሕ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

በሌላ በኩል ሰላማዊት ካሳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ እንዲሁም ሃና አርዓያሥላሴ ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም