ቀጥታ፡

በአፍሪካ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የኢትዮጵያ ጠንካራ ተሳትፎና የመሪነት ሚና ሊቀጥል ይገባል- የናይጄሪያ የመከላከያ ሚኒስትር ተወካይ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2017(ኢዜአ)፦ በአፍሪካ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የኢትዮጵያ ጠንካራ ተሳትፎና የመሪነት ሚና ሊቀጥል ይገባል ሲሉ  የናይጄሪያ የመከላከያ ሚኒስትር ተወካይ ብርጋዴር ጀነራል ናስር ናጋዳዳ ገለጹ።

በዓለም አቀፍና አሀጉራዊ የሰላም ማስከበር ተልእኮ፣ ሽብርተኝነትን በመዋጋት፣ በልማት ትስስር፣ በፓን አፍሪካኒዝም ንቅናቄና ሌሎችም ዘርፎች የኢትዮጵያ ጠንካራ ተሳትፎና ትብብር እስካሁንም ቀጥሏል። 

ከዚሁ ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው የናይጄሪያ የመከላከያ ሚኒስትር ተወካይ ብርጋዴር ጀነራል ናስር ናጋዳዳ፤ ለአፍሪካዊያን ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ በመሻት ኢትዮጵያ በመሪነቷ መቀጠሏን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በጸጥታ ዘርፍ ያካበተችው ልምድና አሁንም የገነባችው ጠንካራ ተቋም አህጉራዊ ተሳትፎዋን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም በአፍሪካ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ የኢትዮጵያ ጠንካራ ተሳትፎና የመሪነት ሚና ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።


 

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ፤ የአፍሪካ አገራት የኢትዮጵያን የመከላከያና የደህንነት የተቋማት ግንባታ በማድነቅ በዘርፉ በትብብር ለመስራት ፍላጎት ማሳየታቸውን ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ልምዷን ለማካፈልና በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም ሚኒስትሯ አረጋግጠዋል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም