ቀጥታ፡

"ሉዓላዊነት በምርታማነት" በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት ዛሬ በአዳማ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 8/2017(ኢዜአ)፦ "ሉዓላዊነት በምርታማነት" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የፓናል ውይይት ዛሬ በአዳማ ከተማ ይካሄዳል።

በፓናል ውይይቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይታደማሉ።

በመድረኩ የምግብ ሉዓላዊነት ከአገር ሉዓላዊነት ጋር ያለው ትስስር፣ ከብሔራዊ አደጋ ስጋት ቅነሳ ፖሊሲ አኳያ ያለው መስተጋብር እንዲሁም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የተመለከቱ መነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።

በኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያሉ ምቹ ሁኔታዎች በውይይቱ በስፋት የሚዳሰሱ ይሆናል።

መድረኩን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት በመተባበር አዘጋጅተውታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም