ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ትልሞች እንዲሳኩ ድጋፍ ማድረጓን ትቀጥላለች - አምባሳደር ሂሩት ዘመነ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ትልሞች እንዲሳኩ ድጋፍ ማድረጓን ትቀጥላለች - አምባሳደር ሂሩት ዘመነ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 7/2017(ኢዜአ):- ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የያዛቸው ውጥኖች ከዳር እንዲደርሱ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን በሕብረቱ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ገለጹ።
በአፍሪካ ሕብረት እና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት ዛሬ አቅርበዋል።
ሁለቱ ወገኖች የአፍሪካ ሕብረትን እያደረገ ያለውን ተቋማዊ ማሻሻያ አሁናዊ ሁኔታ እና በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ሕብረት ያለውን ትብብር ማጠናከር ላይ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።
አምባሳደር ሂሩት ኢትዮጵያ አፍሪካ ሕብረት የያዛቸው እቅዶች እንዲሳኩ እያደረገ ለሚገኘው ጥረት ድጋፏን አጠናክራ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።