የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ደም ልገሳ አካሄዱ - ኢዜአ አማርኛ
የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ደም ልገሳ አካሄዱ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 7/2017(ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሄዱ።
በሀረሪ ክልል ሁለተኛ ዙር ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በደም እጦት የተቸገሩ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ የደም ልገሳ አካሂደዋል።
መርሀ ግብሩ “ደማችን ለወገናችን” በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደ ሲሆን ለተለያዩ አደጋዎች የተጋለጡ ብሎም በወሊድ ምክንያት ደም የሚያስፈልጋቸውን እናቶች ህይወት ለመታደግ መለገሳቸውን አመራሮቹ ገልፀዋል።
ደም መለገስ የዜጎችን ህይወት መታደግ መሆኑን የገለፁት አመራሮቹ በቀጣይም የደም ልገሳውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።