በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ 519 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ - ኢዜአ አማርኛ
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ 519 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 7/2017(ኢዜአ):- በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሶስት ወራት ወደ ውጭ አገራት ከተላከ ቡና 519 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።
በሩብ ዓመቱ 115 ሺህ 851 ቶን በላይ የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ምርት ወደ ውጭ በመላክ 522 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ መገኘቱን ገልጿል።
ከገቢው ከፍተኛ ድርሻ የያዘው የቡና ምርት ነው።
በተጠቀሰው ጊዜ 115 ሺህ 174 ነጥብ 75 ቶን ቡና በመላክ 519 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱ ተገልጿል።
ይህም በ2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተላከው ጋር ሲነጻጸር በመጠን 69 በመቶ እና በገቢ የ46 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።