ዛሬ የኢትዮ ቴሌኮም አክስዮን ለሽያጭ ዝግጁ መሆኑን ያበሰርንበት የታሪካዊ ክንውን ምዕራፍ እለት ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2017(ኢዜአ)፦ ዛሬ የኢትዮ ቴሌኮም አክስዮን ለሽያጭ ዝግጁ መሆኑን ያበሰርንበት የታሪካዊ ክንውን ምዕራፍ እለት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ስድስት አመታት ከፖለቲካዊ አብዮት ወደ የለውጥ መንገድ እያደረግነው ያለነው ስኬታማ ጉዞ ማሳያ ነውም ሲሉ ጠቁመዋል።

እንደ ዲጂታል ኢትዮጵያ ያሉ ቁልፍ የለውጥ ሥራዎች መተግበራቸው ለዛሬው ታሪካዊ ሁነት ፅኑ መደላድል ፈጥረዋል ብለዋል።


 

በተለያዩ ዘርፎች የሚታይ እድገትን ማስቻለቸውንም እንዲሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 50 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን የገንዘብ ዝውውር ተግባራቸውን በሞባይል እንደማከናወናቸው የ130 አመታት ዕድሜ ባለፀጋው ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ የአክስዮን ድርሻውን በሽያጭ ለሕዝብ አቅርቧል ሲሉም አብስረዋል።

ይህ ለኢትዮጵያ የአክስዮን ገበያ መደላድል የሚፈጥር ብሎም በሀገራችን ካሉ ቀዳሚ መንግሥታዊ የንግድ ተቋማት(አሁን ወደ አክስዮን ድርጅትነት የተለወጠ) አንዱ ከሆነው ከአንጋፋው ኢትዮ ቴሌኮም የባለቤትነት እድልን የሚያሰፋ ክንዋኔ ነው ሲሉ ገልጸው፤ ሁላችንም እንኳን ደስ አለን ብለዋል በመልዕክታቸው።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም