ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ አክሲዮን ሽያጭን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮ-ቴሌኮም 10 በመቶ አክሲዮን ሽያጭን በይፋ አስጀምረዋል።

የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌ ብር አማካኝነት ኢትዮጵያዊያን መግዛት እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ፣ የኢትዮጵያ ዲጂታል ጉዞ ባለፉት 6 ዓመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተከናወኑ የለውጥ ስራዎች ስኬት መሰረት የጣለ መሆኑን ተናግረዋል።


 

በዚህም ኢትዮጵያ በዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ፣ በዲጂታል ግብይት እንዲሁም በሃይል ልማት ከፍተኛ ስራ መስራቷን አንስተዋል።

በዛሬው እለትም የኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻን ለኢትዮጵያውያን በመሸጥ የአክሲዮኑ ገበያ በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።

የቴሌኮም አክሲዮን ሽያጩ ኢትዮጵውያን ባሉበት ቦታ ሆነው በሀገራቸው ኢንቨስት በማድረግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም