ቀጥታ፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሐዘን ገለጸ

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 6/2017(ኢዜአ)፦የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፦ የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር በነበሩት ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሐዘን ገልጿል።

የቀድሞ የምክር ቤት አባል ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ፥በ4ኛ እና በ5ኛ ዙር በምክር ቤቱ በአባልነት በመመረጥ በተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች በሰብሳቢነት ማገልገላቸውን ምክር ቤቱ ገልጿል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገልጾ፦ ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም