ለማረፍ ሲዘጋጅ ጭስ የታየበት አውሮፕላን በተሳካ ሁኔታ ማሳረፍ መቻሉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
ለማረፍ ሲዘጋጅ ጭስ የታየበት አውሮፕላን በተሳካ ሁኔታ ማሳረፍ መቻሉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጸ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 6/2017 (ኢዜአ)፡- በድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ ጭስ የታየበት አውሮፕላን በሰላም ማረፉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡
ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 አውሮፕላን ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ ጭስ መታየቱ ተገልጿል፡፡
አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ በሰላም በማረፍ መንገደኞችን በተለመደው መልኩ ከአውሮፕላኑ ማውረድ መቻሉን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡
አየር መንገዱ ጭሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ገልጾ ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል፡፡