ቀጥታ፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጌታቸው መለሰ(ዶ/ር) ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2017(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ጌታቸው መለሰ(ዶ/ር) ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ መልዕክት የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ጌታቸው መለሰ(ዶ/ር) በማለፋቸው የተሰማኝን ጥልቅ ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር ሲሉም ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም