ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2017(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር በነበሩት ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ መልዕክት ለሟች ቤተሰቦች፣ ሥራ ባልደረቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

ጌታቸው መለሰ (ዶ/ር) ባጋጠማቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም