ዓለም አቀፍ የታዳጊዎች የሜዳ ቴኒስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ መካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
ዓለም አቀፍ የታዳጊዎች የሜዳ ቴኒስ ሻምፒዮና በኢትዮጵያ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 4/2017 (ኢዜአ) ፦ ዓለም አቀፍ የታዳጊዎች የሜዳ ቴኒስ (J30) ሻምፒዮና ዛሬ በአዲስ አበባ ቴኒስ ክለብ መካሄድ ጀምሯል።
ሻምፒዮናውን የኢትዮጵያ ቴኒስ ፌዴሬሽን ከዓለም አቀፉ ቴኒስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ነው።
በሻምፒዮናው ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሲሆን ከ16 ሀገራት የተወጣጡ 19 ሴትና 32 ወንድ ስፖርተኞች በአጠቃላይ 51 ስፖርተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
አሜሪካ፣ ጣልያን፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ብራዚል፣ ሕንድ፣ ኮሪያ ሪፐብሊክ፣ ጃፓን እና ኬንያ ከተሳታፊ ሀገራት መካከል ይጠቀሳሉ።
ውድድሩ በኢትዮጵያ መካሄዱ በስፖርቱ ዘርፍ መነቃቃትን በመፍጠር ሀገርን ሊወክሉ የሚችሉ ስፖርተኞችን ለመፍጠር እንደሚያስችል ተመላክቷል።
የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ እንዲገነባ፤ የስፖርቱን ቱሪዝም ለማሳደግና ውድድሩ ገቢ ለማመንጨት ፋይዳ እንዳለውም ተገልጿል።
ዓለም አቀፍ የታዳጊዎች የሜዳ ቴኒስ ሻምፒዮና እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቆይ ከባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።