የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የነፃነት ትግል መሰረትና የፓን አፍሪካኒዝም ምልክት ነው - አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የነፃነት ትግል መሰረትና የፓን አፍሪካኒዝም ምልክት ነው - አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 4/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የነፃነት ትግል መሰረትና የፓን አፍሪካኒዝም ምልክት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ።
ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረው ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ በመላ ሀገሪቱ ተከብሯል።
እለቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኤምባሲዎችና ሚሲዮኖች በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፤ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የነፃነት ትግል መሰረትና የፓን አፍሪካኒዝም ምልክት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
እለቱ የሚከበረው ለሀገር ሉዓላዊነት በጀግንነት የተከፈለን መስዋዕትነት በማሰብ ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞን ዳር ለማድረስ በመዘጋጀት መሆኑንም አንስተዋል።