ቀጥታ፡

በብዝሃነታችን ዉስጥ ያለውን አንድነትና አብሮነት ይበልጥ በማጠናከር ለዘላቂ ሰላምና ልማት ተግተን ልንሰራ ይገባል - ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ

ጋምቤላ ጥቅምት 4/2017(ኢዜአ)፦ሰንደቅ ዓላማችን በብዝሃነታችን ዉስጥ ያለዉን አንድነትና አብሮነት ይበልጥ በማጠናከር ለዘላቂ ሰላምና ልማት ተግተን ልንሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ገለፁ።

“ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ’’ በሚል መሪ ሃሳብ 17ኛው ብሔራዊ የሰንቅ ዓለማ ቀን ጋምቤላ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ዛሬ በድምቀት ተከብሯል ።


 

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድ በክብረ በዓሉ ላይ እንዳሉት ሰንቅ ዓላማ የኢትዮጵያ ህዝቦች የህብር ብሔራዊ አንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ አርማ ነው።

ብሔራዊ ሰንቅ ዓላማ የኢትዮጵውያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ለተዋደቁላት ህያው ምልክት ከመሆኑም በላይ የድል አድራጊነት መግለጫ አርማ ጭምር መሆኑንም ተናግረዋል።

የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በየዓመቱ የሚከበረው በመርሆዎቹና ለብዝሃነት ባለው ትርጉም ዙሪያ ለማህበረሰቡ በተለይም ለወጣቱ ትውልድ የጠራ ግንዛቤ ለማስጨበጥ መሆኑንም ተናግረዋል።

በመሆኑም የሰንቅ ዓላማ ፍቅርና ክብር በመጠበቅ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማራጋገጥ ሁሉም ዜጋ በአንድነት ሊሰራ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሯ አሳሰበዋል።

የሰንቅ ዓላማ ፍቅርና ክብር በመጠበቅ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማራጋገጥ ሁሉም ዜጋ በአንድነት ሊሰራ እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሯ አሳሰበዋል።

በጋምቤላ ከተማ በተካሄደው የሰንደቅ ዓላማ ክብረ በዓል በርዕስ መስተዳድሯ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድና በክልሉ ምክር ቤት አፍ- ጉባኤ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በላቀ ቁርጠኝነት ለመፈፀም ቃል ገብተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልልና የፌዴራል የፖሊስ አባላት የሰልፍ ትርኢት አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም