ቀጥታ፡

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተከበረ

አሶሳ፤ ጥቅምት 4/2017(ኢዜአ)፦ 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ተከብሯል።

ቀኑ የተከበረው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሐሰን፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ አስካል አልቦሮ እና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እና የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ነው።

የክልሉ ምክርቤት አፈጉባኤ አስካል አልቦሮ በወቅቱ እንደገለፁት ሰንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር መለያ በመሆኑ ተገቢውን ክብር ልንሰጠው ይገባል።


 

አፈጉባኤዋ የቀኑ መከበር ለሰንደቅ ዓላማ ያለንን ክብር የምንገልጽበት እና ቃላችንን የምናድስበት ነው ብለዋል።

የሁላችንም ኩራት እና መለያ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ በክብር ልንጠብቀው ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ይገኛል።

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም