ቀጥታ፡

ትምህርት ቤቶች ማህበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣ ትውልድ የመገንባት ድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

አዳማ ፤ ጥቅምት 3/2017(ኢዜአ)፦ ትምህርት ቤቶች ደም ልገሳን በማበረታታት ማህበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣ ትውልድ የመገንባት ድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።

የኢትዮጵያ የደምና ህብረህዋስ ባንክ አገልግሎት የደም ልገሳን አላማ ያደረገ የትምህርት ተቋማት የጋራ ውይይት መድረክ በአዳማ ከተማ አካሂዷል ።

የአገልግሎቱ  ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ በወቅቱ እንደገለጹት ትምህርት ቤቶች ደም ልገሳን በማበረታታት ማህበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣ ትውልድ የመገንባት ድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል።

በተጠናቀቀው 2016 በጀት አመት እንደ ሀገር ከተሰበሰበው 349 ሺህ ዪኒት ደም 51 በመቶው ከትምህርት ቤቶች የተሰበሰበ መሆኑን ጠቁመዋል።

በ2017 በጀት አመት ለመሰብሰብ የታቀደውን 513 ሺህ ዩኒት ደም ለማሳካት ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ከደም ልገሳ ጋር ተያይዞ እያጋጠመ ያለውን  የግንዛቤ እጥረት ለመቅረፍ ከትምህርት ሚኒስቴርና ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በቅንጅት ለመስራት መታቀዱን  አስታውቀዋል።

የአገልግሎቱ የደም ለጋሾች መሪ ስራ አስፈፃሚ  ዶክተር መላሽ ገላው በበኩላቸው ትምህርት ቤቶች ደም በመለገስ ህይወት የማስቀጠል በጎ ተግባር ትውልዱን ተሳታፊ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

ትውልዱን በደም ልገሳ ተሳታፊ በማድረግ የማህበረሰብ ተሳትፎንና ባለቤትነትን በማሳደግ ረገድ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

“በትምህርት ቤቶች የበጎ አድራጎት ክበባትን መደገፍና ማንቀሳቀስ ይበልጥ የተማሪዎችን ተሳትፎ የሚያጠናክር በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል “ ያሉት ደግሞ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተገኙት አቶ ቀፀላ ፍቅረማሪያም ናቸው።

የተሻለ ተሞክሮ ያላቸውን አምባሳደር በማድረግ አርአያነትን ማሳየትም ቋሚ የደም ለጋሾችን ለማበራከት የሚረዳ ነው  ሲሉም አክለዋል።

ወላጆችን፣ ተማሪዎችንና መምህራንን ያሳተፈ የውይይት መድረክ መፍጠር የግንዛቤ ማስጨበጫውን  ይበልጥ ተደራሽ እንደሚያደርገው አመልክተዋል ።

የቀኝ አዝማች አንዳርጌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት መስከረም ክበበው በበኩላቸው እንደ ሚዲያ ካሉ ተቋማት  ጋር በቅንጅት መስራት የለጋሾችን ቁጥር ለማበራከት የሚረዳ መሆኑን ጠቁመዋል።

በውይይት መድረኩ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮና  ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ባለድርሻዎች ተሳትፈዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም