የሁለተኛ ዙር የአመራሮች አቅም ግንባታ ሰልጣኞች የፌደራል ፖሊስን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የሁለተኛ ዙር የአመራሮች አቅም ግንባታ ሰልጣኞች የፌደራል ፖሊስን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2017(ኢዜአ)፦ "የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት'' በሚል መሪ ሀሳብ እየተሰጠ ያለው የሁለተኛ ዙር የአመራሮች አቅም ግንባታ ሰልጣኞች የፌደራል ፖሊስን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ እንዲሁም ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ተገኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፌደራል ፖሊስ የተቋም ግንባታ ምን ማለት እንደሆነ በተግባር ያሳየ መሆኑን ገልፀዋል።
እንደ ከተማ የተጀመሩ የለውጥ ሥራዎችን ማስፋትና ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ከሀገራዊ ለውጡ በኃላ በፌደራል ፖሊስ በተከናወነ የሪፎርም ሥራ ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት መፈጸም በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲሆን አድርጓል።
ከ2010 ዓ.ም በኋላ ተቋሙ እራሱን በቴክኖሎጂ በማደራጀት ወቅቱን በዋጀ መልኩ እየተሸጋገረ መሆኑንም አንስተዋል።
ዛሬ ላይ የፌደራል ፖሊስ ጠንካራ የጸጥታ ተቋም መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ እንደሆነም ጠቁመዋል።