ሰልጣኝ አመራሮች በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ሰልጣኝ አመራሮች በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

ቦንጋ፤ ጥቅምት 3/2017(ኢዜአ)፦ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተከታተሉ የሚገኙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።
"የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ እድገት' በሚል መሪ ሀሳብ 2ኛ ዙር የአመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ በቦንጋ ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።
በስልጠናው የክልሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ሰልጣኝ አመራሮቹ በዛሬው ዕለት በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ በተቀናጀ መንገድ በመከናወን ላይ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት በሌሎች የክልል ከተሞችም እየተተገበረ ይገኛል።
በዚህም ሰልጣኝ አመራሮቹ በቦንጋ ከተማ እየተከናወነ የሚገኘውን የከተማ ኮሪደር ልማት ስራ አመራሮቹ ምልከታ በማድረግ ላይ ናቸው።
በተጨማሪም አባይነሽ ፋርምና በክላስተር ማዕከል የተለያዩ ኢንተርፕራይዞችን የስራ እንቅስቃሴና ሌሎች የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙ ከወጣው መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል።