የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ ሰልጣኝ አመራሮች በወላይታ ሶዶ ከተማ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን እየጎበኙ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ ሰልጣኝ አመራሮች በወላይታ ሶዶ ከተማ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን እየጎበኙ ነው

ሶዶ፤ ጥቅምት 3/2017(ኢዜአ)፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው እየጎበኙ ነው።
አመራሮቹ ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 8/2017 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ የአቅም ግንባታ ስልጠና በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከታተሉ ነው።
አመራሮቹ በተለያየ ቡድን በመሆን በወላይታ ዞን ሶዶና ቦዲቲ ከተማ አስተዳደሮች እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ነው እየተመለከቱ የሚገኙት።
በጉብኝታቸው በተቀናጀ መንገድ እየተከናወኑ ያሉ የመሰረተ ልማትና ሌሎች የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ የሚገኙና ውጤታማ የሆኑ የልማት ተግባራትን እንደሚመለከቱ ተገልጿል።
በአሁኑ ሰዓት በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ትሩፋት፣ የሰብል ልማት፣ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት፣ አረንጓዴ አሻራና ሌሎች የልማት ሥራዎችን የመስክ ምልከታ እያደረጉ ይገኛሉ።