ብርቱ እጆች፣ የማይዝሉ ክንዶች እና የሚያሰላስሉ አዕምሮዎች የዕድገት አየር የሚነፍስባቸውን ከተሞች ይገነባሉ -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
ብርቱ እጆች፣ የማይዝሉ ክንዶች እና የሚያሰላስሉ አዕምሮዎች የዕድገት አየር የሚነፍስባቸውን ከተሞች ይገነባሉ -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2/ 2017 (ኢዜአ)፦ ብርቱ እጆች፣ የማይዝሉ ክንዶች እና የሚያሰላስሉ አዕምሮዎች የዕድገት አየር የሚነፍስባቸውን ከተሞች ይገነባሉ ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ በባህር ዳር ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችንና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ጎብኝተናል ብለዋል፡፡
በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ባህር ዳርን ወደተሻለ የከተማነት ደረጃ የሚያሸጋግሩ እና የነዋሪዎችን ህይወት የሚያሻሽሉ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል፡፡