የጋምቤላ ክልልን እምቅ የልማት አቅም በማልማት የገበያ ትስስር ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል - ኢዜአ አማርኛ
የጋምቤላ ክልልን እምቅ የልማት አቅም በማልማት የገበያ ትስስር ለመፍጠር በትኩረት ይሰራል

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 2/2017(ኢዜአ)፦የጋምቤላ ክልልን እምቅ የመልማት አቅም በማልማት እና ለምርቱም የገበያ ትስስር ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ዶ/ር ገለጹ።
ሚኒስትሩ በዛሬው እለት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ እና ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
ሚኒስትሩ በአቦቦ ወረዳ ሉንጋ ቀበሌ እና በአቦቦ ከተማና ሌሎች የክልሉ የተለያዩ እምቅ የልማት አቅሞችን ጎብኝተዋል።
በዚህም ክልሉ እምቅ የልማት አቅም ያለው በመሆኑ በማምረት እና የተመረተውን ምርት ለገበያ ለማቅረብ ሰፊ የገበያ ትስስር እንደሚሰራ መግለጻቸውን ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።