በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ የማህበረሰቡን ኑሮ ለማሻሻል እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው - ኢዜአ አማርኛ
በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ የማህበረሰቡን ኑሮ ለማሻሻል እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው

አሶሳ፣ጥቅምት 2/2017(ኢዜአ)፦በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ የማህበረሰቡን ኑሮ ለማሻሻል እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው ሲሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ተናገሩ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ፥በወረዳው የሌማት ቱሩፋት ውጤት አንዱ የሆነው የንብ ማነብ ስራ በማህበረሰቡ ተነሳሽነት የተሰራ መሆኑን ገልጸው፥ ይህም ተጠናክሮ ሊሰራበት ይገባል ብለዋል፡፡
የግብርናውን ዘርፍ በማሳደግ ማህበረሰቡ በተለያዩ የሌማት ስራዎች እንዲሰማራ ማድረግም የሁሉንም ርብርብ የሚጠይቅ ነው ሲሉ አቶ አሻድሊ ጠቁመዋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በግብርናው ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ የማህበረሰቡን ኑሮ ለማሻሻል እየተሰራ ያለው ስራም አበረታች ነው ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ባለፉት ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር የተተከሉ ችግኞች ያሉበትን ቁመና በአብራሞ ወረዳ ተገኝተውም የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡
ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ማንጎ፣ አቮካዶ እንዲሁም ቀርቀሀ እና ገረቢላ ችግኞች በወቅቱ የተተከሉ መሆናቸውን የጠቆሙት አቶ አሻድሊ፥ቀጣይም ከ2 እና 3 ዓመታት በኋላ ምርት የሚሰጡበት ሁኔታ እንዳለ አመላካች ነው ማለታቸውን ብለዋል፡፡
የቤኒሻንጉል ግሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ፣ በግብርናው ዘርፍ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር በመከተልም በየዓመቱ በክልሉ 50 ሚሊየን ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም በአብራሞ ወረዳ በመንገሌ 38 እና 39 ቀበሌዎች የተሰሩት የልማት ስራዎች ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ከመስጠታቸው ባለፈ አካባቢን በደን ለመሸፈን ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ነው ሲሉ አቶ ባበክር አብራርተዋል፡፡
የአብራሞ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ያሲን ሀሰን በበኩላቸው፣ ማህበረሰቡ ግብርናውን ለማዘመን በተለያዩ የልማት ስራዎች ተሰማርቶ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ በኩልም የማህበረሰቡ ተሳትፎ የጎላ ነው ማለታቸውን ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡