በሶማሌ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ሰኞ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
በሶማሌ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ሰኞ ይጀመራል

አዲስ አበባ ፤ጥቅምት 2/2017 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሶማሌ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ሰኞ ጥቅምት 4 ቀን 2017 እንደሚጀምር አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ለሚያካሂደው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ በጅግጅጋ፣ ጎዴና ዶሎ አዶ ከተሞች የግንዛቤ ማስጨበጫና የቅስቀሳ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።