የኢትዮጵያና ሞሮኮ ፖሊስ ተቋማት በጋራ መሥራት የሚያስችል ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2/ 2017 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያና ሞሮኮ ፖሊስ ተቋማት በጋራ መሥራት የሚያስችል ውይይት አካሂደዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ከሞሮኮ የግዛት ቁጥጥር ዋና ዳይሬክተር ምክትል ኃላፊና የሀገሪቱ ፖሊስ ኢንተለጀንስ ዳይሬክተር ፋራሀ ቦውልሀታህ ውይይት አካሄደዋል፡፡

በውይይቱም፥ ሁለቱ የፖሊስ ተቋማት በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል።

ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችንና ሽብርተኝነትን ለመከላከል እንዲሁም በሁለቱ የፖሊስ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

የሞሮኮ የግዛት ቁጥጥር ዋና ዳይሬክተር ምክትል ኃላፊና የሀገሪቱ ፖሊስ ኢንተለጀንስ ዳይሬክተር በበኩላቸው፥የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የደረሰበትን ሁሉን አቀፍ የዘመነ የፖሊስ አገልግሎትና የታጠቃቸውን ቴክኖሎጂዎች አድንቀዋል፡፡

አክለውም፥ የሁለቱ ሀገራት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ የረጅም ጊዜ ግንኙነት በፖሊስ ሥራዎችም ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም