ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባህር ዳር ከተማ የተገነቡ የልማት ስራዎችን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባህር ዳር ከተማ የተገነቡ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2017(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባህር ዳር ከተማ የተገነቡ መናፈሻዎችንና ግዙፉን የአባይ ድልድይ ጎብኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በውቢቷ ባህር ዳር የተገነቡ መናፈሻዎችን እንዲሁም ግዙፉንና አስደማሚውን የአባይ ድልድይ ጎብኝተናል ብለዋል።
እነዚህ የልማት ስራዎች እጅግ ውብ እና ማራኪ ናቸው። ለህዝባችን እንዲሁም ከሩቅም፥ ከቅርብም ለሚመጡ ቱሪስቶች ማረፊያና መዝናኛነት ምቹ የሆኑ ከተሞችን ለመገንባት እየሰራን መሆኑን ማረጋገጫ አሻራዎች ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።