ቀጥታ፡

አምስተኛው ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ወር በሳይንስ ሙዚየም መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 1/2017 (ኢዜአ)፦ አምስተኛው ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ወር በሳይንስ ሙዚየም መካሄድ ጀመረ።

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ " የቁልፍ መሠረተ ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት " በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚካሄደው። 

በመርኃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፣ ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ፣ የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የሳይበር ደህንነት ወር እንደ ሀገር ከ2012 ጀምሮ በየዓመቱ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን ወሩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ ነው የሚከበረው።

በሳይበር ደህንነት ወር ላይ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርኃ ግብሮች እንደሚካሄዱም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም