ታማኝ ግብር ከፋዮች የዜግነት ግዴታችሁን ለመወጣት ያደረጋችሁት ቁርጠኝነት ምስጋና የሚገባው ነው -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2017(ኢዜአ):- ታማኝ ግብር ከፋዮች የዜግነት ግዴታችሁን ለመወጣት ያደረጋችሁት ቁርጠኝነት ምስጋና የሚገባው ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የ6ኛው የታማኝ የግብር ከፋዮች ሽልማት ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

የዜግነት ግዴታችሁን ለመወጣት ያደረጋችሁት ቁርጠኝነት ምስጋና የሚገባው ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ታማኝነት ከግለሰብ ይጀምራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ግብር መክፈል ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን የዚያ እምነት መገለጫም ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው ለበለጠ ጥቅም ሁላችንም የምንካፈለው ግዴታችንም ነው ብለዋል።

ለታማኝነታችሁ መንግስት የከፈላችሁት ግብር በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ ለጋራ እድገታችን ወሳኝ በሆኑ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባሉ ግዙፍ የሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ አስተዋፅዖችሁን በማዋል ይህንን አደራ ያከብራል ሲሉም ገልጸዋል።

በግብር አሰባሰብ ላይ አወንታዊ ለውጦች እየታዩ ቢሆንም፣ ይህን ጥሩ ጅማሮ ማስቀጠል ይኖርብናል። ሙስናን መቀነስ እና የግብር አሰባሰብ ስርዓታችንን ማዘመን ለሁሉም የተመቸ፣ ግልፅ፣ ቀልጣፋ እና ፍትሃዊ አሰራር ለመፍጠር ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም