የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መሪዎች ለፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መሪዎች ለፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2017(ኢዜአ)፦ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መሪዎች አዲስ ለተሰየሙት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የደስታ መልዕክቱን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱምን ጨምሮ ሌሎች የሀገሪቱ ከፍተኛ መሪዎች ማስተላለፋቸውን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡