የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 30/2017(ኢዜአ) ፡- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ምክር ቤቱ እያደረገ ባለው ስብሰባ የምክር ቤቱን 3ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ አጽድቋል።
የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ፣ የኢትዮጵያ የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ፣ የመድኃኒት ፈንድና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትን ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር፤ እንዲሁም የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ምክር ቤቱ ካወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል።