የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያደርጋል - ኢዜአ አማርኛ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያደርጋል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2017(ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።
ምክር ቤቱ በስብሰባው የምክር ቤቱን 3ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ እንደሚያፀድቅ ገልጿል።
ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ፣ የኢትዮጵያ የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ፣ የመድኃኒት ፈንድና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎትን ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራም ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር፤ እንዲሁም የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።