የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ ከአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኢመስበርገር ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ ከአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኢመስበርገር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ ከአውሮፓ ሕብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም-ኢመስበርገር ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ለአምባሳደር ሶፊ በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት አሁናዊ ተግባራት በተመለከተ በኮሚሽነሮች ገለጻ እና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
አምባሳደሯ በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የምክክር ሂደት አድንቀው የጀመሩትን የትብብር ማዕቀፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በቀጣዮቹ ጊዜያትም ኮሚሽኑ ነፃነቱን እና ገለልተኝነቱን በጠበቀ መልኩ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር እንደሚሰራ መግለጻቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።