ቀጥታ፡

በአዲስ አበባ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ዘመቻ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 29/2017(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ በሁሉም ወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ዘመቻ ይካሄዳል።

ዘመቻውን አስመልክተው የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ዮዳሄ አርዓያሥላሴ እና የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዮናስ አለማየሁ በጋራ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም በሁሉም ወረዳዎችና ክፍለ ከተሞች እንዲሁም የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና መሥሪያ ቤት እና ሁለት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የፋይዳ ምዝገባ ከነገ ጀምሮ በዘመቻ መልክ እንደሚያከናውን ተገልጿል።

ዘመቻው ማኅበረሰቡ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓትን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል ተመልክቷል።

ከተማ አቀፍ የምዝገባ ሥራውን ለማሳለጥ ይረዳ ዘንድ ሁለቱ ተቋማት የጋራ ግብረ-ኃይል አቋቁመው ዝግጅት ማድረጋቸው ነው በመግለጫው የተገለፀው።

ዘመቻው በከተማ ደረጃ የተጀመረውን የዲጂታል አገልግሎት በማስቀጠልና የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋ እንዲሆኑ ያግዛል ነው የተባለው።

በከተማዋ ነዋሪ የሆኑ እንዲሁም ነዋሪ ያልሆኑ ግለሰቦች በእነዚህ ጣቢያዎች ተገኝተው እንዲመዘገቡ የሁለቱ ተቋማት ኃላፊዎች ጥሪ አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም