ኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች መጠለያ ናት- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች መጠለያ ናት- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 28/2017 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች መጠለያ ናት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ከተባበሩት መንግስታት የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (UN-IOM) ዳይሬክተር ጄነራል ኤሚ ፖፕ ጋር ውይይት አድርገናል ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ ተመስገን ጥሩነህ ከተቋሙ ጋር በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ መምከራቸውንም አስታውቀዋል፡፡
በዚህም የህገ ወጥ ፍልሰት ተግዳሮቶችን በዘላቂነት መፍታት እና የውጪ ሀገር ስራ ስምሪት ለዘላቂ ልማት የሚያበረክተዉን አስተዋፅዖ ማሳደግ በሚቻልባቸው የትብብር ሀሳቦች ላይ ከስምምነት ደርሰናል ብለዋል።
የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ህገወጥ ፍልሰትን ከመከላከል፣ ከፍልሰት ተመላሾች እና ተፈናቃዮችን ከመደገፍ አኳያ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፡፡