የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆኜ በመመረጤ ልዩ ክብር እና ኩራት ይሰማኛል - ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀስላሴ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆኜ በመመረጤ ልዩ ክብር እና ኩራት ይሰማኛል - ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀስላሴ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 28/2017(ኢዜአ)፦ ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀስላሴ አምስተኛው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው የተለየ ክብር እና ኩራት እንደሚሰማቸው ገለጹ።
ፕሬዚደንቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ታላቋን እና ተወዳጇን ሀገር እንዳገለግል ትልቅ እምነት ስለጣሉብኝ ላመሰግናቸው እወዳለሁ ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ትናንት በተካሄደበት ወቅት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴን ፕሬዝዳንት አድርጎ መምረጡ ይታወቃል።
ፕሬዚደንት ታዬ አጽቀስላሴ ሁለቱ ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን በማብሰር የፌዴራል መንግሥቱን ዓመታዊ ዕቅድ አቅርበዋል።