ተመድ ከኢትዮጵያ ጋር በልማቱ መስክ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ - ኢዜአ አማርኛ
ተመድ ከኢትዮጵያ ጋር በልማቱ መስክ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/20 (ኢዜአ)፦የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከኢትዮጵያ ጋር በልማቱ መስክ ያለውን ትብብር አጠናክሮ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን አስታወቀ።
ተመድ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው ለተመረጡት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፏል።
ኢትዮጵያ እና ተመድ ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት እንዳላቸውና አገር በቀል መፍትሔዎችን መሰረት በማድረግ የልማት ስራዎችን እየደገፈ እንደሚገኝ ተመድ ገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የልማት ትብብር እና ዘላቂ የልማት ግቦቹን ለማሳካት እያደረገች ያለውን ጥረት መደገፉን በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል አመልክቷል።
የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከተመድ ጋር ለነበራቸው ትብብር እና አጋርነት ለሁለቱ ወገኖች የጋራ ትብብር መጠናከር ላደረጉት አስተዋጽኦም ተመድ ምስጋናውን ገልጿል።
ተመድ ይህንኑ ትብብሩን ከአምባሳደር ታዬ ጋር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በይፋዊ ገጹ ባወጣው መልዕክት አስታውቋል።