የፓን አፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፍረንስ ነገ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የፓን አፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፍረንስ ነገ ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017 (ኢዜአ) ፦ የፓን አፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፍረንስ ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዩት አስታወቀ።
በአድዋ ድል መታሰቢያ ለሁለት ቀናት የሚካሄደው ኮንፍረንስ "አፍሪካን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማላቅ" በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚከናወን ገልጿል።
ኮንፍረንሱ ለሶስተኛ ጊዜ እንደሚካሄድና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉበት ከኢኒስቲትዩቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።