የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በዩጋንዳ አቻው ተሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በዩጋንዳ አቻው ተሸነፈ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017 (ኢዜአ) :- የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በ24ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ 3 ለ 0 ተሸንፏል።
በምድብ 2 የምትገኘው ኢትዮጵያ ሁለተኛ ጨዋታዋን መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከደቡብ ሱዳን ጋር በኪኖንዶኒ ሙኒሲፓል ካውንስል ስታዲየም ከቀኑ 1 ሰዓት ላይ ታደርጋለች።
በዚሁ ምድብ ዛሬ ቀን ላይ በተካሄደ ጨዋታ ብሩንዲ ደቡብ ሱዳንን 1 ለ 0 አሸንፋለች።
በታንዛንያ የሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ትናንት መጀመሩ ይታወቃል።
በምድብ 1 ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሱዳን ጅቡቲን 3 ለ 1 እንዲሁም ኬንያ አዘጋጇን ታንዛያን 2 ለ 1 አሸንፈዋል።
የማጣሪያ ውድድሩ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በውድድሩ ለፍጻሜ የሚደርሱ ሁለት ሀገራት ለአፍሪካ ዋንጫ ያልፋሉ።