የ2017 በጀት ዓመት የመንግስት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች

አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦ የ2017 በጀት ዓመት የመንግስት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች።

ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ልማትን በስፋት ማከናወን

የገንዘብ ፖሊሲን ውጤታማነት ማስቀጠል

የሀገር ውስጥ የገቢ አማራጮችን በማስፋት ዓመታዊ ገቢን 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ማድረስ

የመንግስት ወጭዎች ውጤታማ እንዲሆኑ እንዲሁም የገጠር መንገድና የውሃ ልማት ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ

የገበያ መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋትና የዋጋ ንረትን መቆጣጠር

አዳዲስ ምርቶችን እሴት ጨምሮ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከሸቀጦች የወጪ ንግድ 5 ቢሊየን ዶላር ማግኘት

አጠቃላይ ከወጪ ንግድ 10 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት 

የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማድረስ

የውጭ አገራት የስራ እድሎችን ማስፋት፣ ሰላምና ፀጥታን በዘላቂነት ማስጠበቅና ቀጣናዊ ትብብርን ማሳለጥ

በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ አማራጭ የባህር በር እንዲኖራት የዲፕሎማሲ ጥረቱን አጠናክሮ መቀጠል

በቀጣናው ዘላቂ ብሄራዊ ጥቅምን ማስጠበቅና የኢትዮጵያን ተደማጭነትና ተጽእኖ ፈጣሪነት ማሳደግ

በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ የዲፕሎማሲ ትብብሮችን ማጠናከር እንዲሁም ቀጣናዊ የልማት ትስስሮችን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል ብለዋል።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

በዚሁ ጊዜ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሰይመዋል። 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም