ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ፕሬዝዳንት ሆነው በመሾማቸው የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው በመሾምዎ እንኳን ደስ ያለዎት ሲሉ አስፍረዋል።

በቀጣይ የስራ ዘመናቸውም ፕሬዝዳንቱ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ከንቲባዋ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም