የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከነጠላ የእድገት ዘርፍ ወደ ብዝሃ ኢኮኖሚ እድገት እየተሸጋገረ ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከነጠላ የእድገት ዘርፍ ወደ ብዝሃ ኢኮኖሚ እድገት እየተሸጋገረ ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017 (ኢዜአ) ፡- የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከነጠላ የእድገት ዘርፍ ወደ ብዝሃ ኢኮኖሚ እየተሸጋገረ እንደሚገኝ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ ገለጹ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ የሁለቱን ምክር ቤቶች ጉባዔ በይፋ ከከፈቱ በኋላ በአዲሱ በጀት ዓመት በመንግሥት የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ንግግር እያደረጉ ይገኛል።
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸውም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ የታሪክ እጥፋት ላይ ይገኛል ብለዋል።
ኢኮኖሚው እውን እና ገበያ መር በማድረግ በዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆን ከነጠላ እድገት ዘርፍ ወደ ብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ እየተሸጋገረ መሆኑን አመልክተዋል።
በዚህም የዜጎች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ መሰረት እየጣለ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የኢኮኖሚ ለውጡ በ10 ዓመቱ የልማት እቅድ ውስጥ ትኩረት የተሰጣባቸው ጥቅል አገራዊ ምርታማነት እና ኢኮኖሚ እድገትን ማሳለጥ ጥሩ አፈጻጸም እያስመዘገቡ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።