አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2017 (ኢዜአ) ፡- አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል።


 

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

አምባሳደር ታዬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሾማቸው በፊትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም