በአፋር ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ሲሳተፉ የቆዩ ተወካዮች አጀንዳዎችን ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከቡ - ኢዜአ አማርኛ
በአፋር ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ሲሳተፉ የቆዩ ተወካዮች አጀንዳዎችን ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከቡ
ሠመራ ፤ መስከረም 27/2017(ኢዜአ):- በአፋር ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ሲሳተፉ የቆዩ ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት የክልሉን አጀንዳዎች አደራጅተው ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አስረከቡ።
በክልሉ ላለፉት ስድስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ሂደት ተጠናቋል።
የክልሉን አጀንዳ ለማደራጀት ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላት የተመረጡ 25 ተወካዮች የተሰበሰበውን አጀንዳ አደራጅተው ለኮሚሽኑ አስረክበዋል።
የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሸነር አምባሳደር አይሮሪት መሐመድ(ዶ/ር) ባለፉት ስድስት ቀናት በክልሉ አካታችና አሳታፊ የአጀንዳ ማሰባሰብ ውይይት ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
በዚህም ለአገራዊ ምክክሩ የሚሳተፉ ወኪሎች መመረጣቸውን ገልጸው፤ ወኪሎቹም አጀንዳውን አደራጅተው ለኮሚሽኑ ማስረከባቸውን ገልጸዋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሸነር ብሌን ገብረመድህን በበኩላቸው በዚሁ የማጠቃለያ መድረክ እንደገለፁት ለዚህ አገራዊ የምክክር ሂደት መሣካት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ያደረጉትን የመንግስት አካላት፣ ሰመራ ዮኒቨርሲቲንና በጎ ፍቃደኞችን አመስግነዋል።