ቀጥታ፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ በመሰራት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ግንባታዎችን ተዘዋውረው ተመለከቱ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2017 (ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በትላንትናው እለት በከተማዋ በመሰራት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ግንባታዎችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ገለጹ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በትላንትናው እለት በከተማችን በመሰራት ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶቻችንን ግንባታዎች ተዘዋውረን ገምግመናል ብለዋል።


 

በተለይም ከተማችንን የኮንፍረንስ፣ የቱሪዝም እና የስበት ማዕከል ለማድረግ የጀመርነውን ጥረት የሚያረጋግጡ፣ የኢኮኖሚ መነቃቃትን የሚፈጥሩ እንዲሁም ለነዋሪዎቻችን የስራ እድልን በሰፊው የሚፈጥሩ የአዲስ ኢንተርናሽናል የኤግዚቢሽንና የኮንፍረንስ ማዕከል፣ ከዚያ ጋር ተያይዞ እየተሰራ ያለውን የለሚ ፓርክ፣ አየር መንገድ-ጎሮን ከአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ጋር የሚያገናኘዉን መንገድ ግንባታ እና የአረንጓዴ ልማት ስራዎቻችን ያሉበትን ደረጃ ጎብኝተናል ሲሉ ገልጸዋል።

ፕሮጀክቶቹ በተገቢ ጥራት በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ሲሆን በፍጥነት ተጠናቅቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ በቅርበት ክትትል እያደረግን በመስራት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም