ቀጥታ፡

የሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላት ምስጋና ይገባቸዋል - የቱለማ አባገዳ ጎበነ ሆላ

ቢሾፍቱ፣ መስከረም 26/2017 (ኢዜአ) ፦የሆረ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሊ የቱለማ አባገዳ እና የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ጸሐፊ ጎበነ ሆላ ገለጹ።

የሆረ አርሰዲ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ከተማ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን ገልጸዋል።


 

የቱለማ አባገዳ ጎበነ ሆላ፣ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ጀሚላ ሲንቢሩ እና የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አለማየሁ አሠፋ በዓሉ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አባገዳ ጎበነ ሆላ በመግለጫቸው ለሆረ ፊንፊኔ እና ሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በስኬት መጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

የኦሮሞ ህዝብ በዓሉን በአብሮነት ለማክበር ያሳየውን አንድነትም አድንቀዋል።


 

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ጀሚላ ሲንቢሮ በበኩላቸው በርካቶች የታደሙበት የኢሬቻ በዓል በስኬት ተጠናቋል ብለዋል።

በበዓሉ ላይ ከበርካታ ሀገራት የተወጣጡ ዳያስፖራ እና የውጪ ዜጎችም መገኘታቸውን ተናግረዋል።

በዓሉ ያለአንዳች የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አለማየሁ አሠፋ እንዳሉትም፤ የምስጋና፣ የአንድነት እና የአብሮነት በዓል የሆነው ኢሬቻ ተጠናቋል ብለዋል።


 

በዓሉ ከኦሮሞ ህዝብ አልፎ የብሔር ብሔረሰቦች መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል።

የሆረ አርሰዴ ኢሬቻ በዓል የቢሾፍቱ ከተማ በኢኮኖሚው ዘርፍ ተጠቃሚ እንድትሆን ማስቻሉንም ጠቁመዋል።

" ኢሬቻ ለባህላችን ህዳሴ " በሚል መሪ ሐሳብ የተከበረው የ2017 ኢሬቻ በስኬት ተጠናቋል።

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም