ቀጥታ፡

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ያሰለጠናቸውን ወታደሮች አስመረቀ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/ 2017 (ኢዜአ)፦ብላቴ የሚገኘው የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች በዛሬው እለት አስመርቋል።

በምረቃ መርሃ- ግብሩ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪ እና የተኩስ አመራር ኃላፊ ሌተናል ጀኔራል አለምሸት ደግፌ በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ጀኔራል መኮንኖች ፣ ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ታድመዋል።


 

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለውትድርና ሙያ ተመልምለው ስልጠና የወሰዱ መሰረታዊ ወታደሮችም ብቃታቸውን የሚያመላክቱ ወታደራዊ ትርኢቶችን ማሳየታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም