ቀጥታ፡

የሆረ አረሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ እየተከበረ ነው

ቢሾፍቱ ፤መስከረም 26/2017 (ኢዜአ)፦የሆረ አረሰዴ ኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ በመከበር ላይ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና የበዓሉ ታዳሚዎች እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ እያቀኑ ነው።

በአባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች መሪነት ስርአቱ ወደሚፈጸምበት ስፍር ደርሰዋል ።

የበዓሉ ታዳሚዎችም ባህላዊ እሴቱን ተከትለው ስርዓቱን የሚያከናውኑ ይሆናል።


 

ኢሬቻ የኦሮሞ የገዳ ስርዓት መገለጫ ከሆኑት ውስጥ አንዱ ሲሆን፥ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በተለያዩ ቦታዎች በስፋት የሚከበር የባህልና እሴት መገለጫ የምስጋና በዓል ነው።

የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል “ ኢሬቻ ለባህላችን ህዳሴ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ ያለው።

ከሌሊት ጀምሮ በመከበር ላይ ያለው በአሉ በርካቶች ታድመውበታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም